ሜሎሪና

የሕይወት ትልቁ ስኬት አላማን ማወቅና መተግበር ነው

ታሪካዊ የሳይኮሎጂ ልብ ወለድ

.....

photo_2021-08-21_16-57-02

ሜሎሪና

ናሁሰናይ ፀዳሉ

በብዙ አንባቢያን ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈው ሜሎሪና ልብወለድ ታሪካዊ ይዘት ያለው ሥነልቡናዊ ልቦለድ ሲሆን የሰው ልጅ ሞትን ለማሸነፍ በሚያረገው የማያቋርጥ ትግል ውስጥ የኢትዮጵያውያንን ቀደምት ጥበባዊ ሚና የሚተርክና ከፍተኛ የአስተሳሰብ ልዕልናችንን የሚያሳይ መጽሐፍ ነው ፡፡ አቀራረቡም አስተማሪ የሥነልቡና ምክሮችንና ሀሳቦችን ከታሪካዊ ክስተቶች ጋር ደምሮ የያዘ ነው፡፡

ከመጽሐፉ የተወሰዱ ሀሳቦች

‹‹ትልቁ የጦርነት ሥፍራ አእምሮ ነው፤ ትልቁ ድል ደሞ ራስን ማሸነፍ ነው››

ኢትዮጵያዬ ቅደሚ፣ አንቺ ስትቀድሚ ልጆችሽ ደስ ይለናል፡፡ አንቺ ስትለሚ ከስደታችን እናርፋለን፤ አንቺ ስትበለጽጊ ዓለም ሁሉ ወዳንቺ ይመጣል›› እያለች ስታለቅስ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ታቤል በልጅነት አእምሮው ‹ኢትዮጵያ› የሚለውን ስም የያዘው፡፡ ታቤልም ‹‹እንዲህ የምትወድድ፣ የሚታዘንላትና የሚለቀስላት ኢትዮጵያ ማን ነች?›› እያለ መጠየቅ የጀመረው ከዚያ በኋላ ነው፡፡

photo_2021-08-21_17-04-26

Review Us On

ሜሎሪና

ሜሎሪና በሦስት አይነት ቋንቋ

photo_2021-08-21_17-06-16

ሜሎሪና

‹‹ትልቁ የጦርነት ሥፍራ አእምሮ ነው፤ ትልቁ ድል ደሞ ራስን ማሸነፍ ነው››

Melooriinaa

“Dirreen lolaa inni guddaan sammuu namaati, Injifannoo guddaan of mo’uudha”

Melorina

"Mind is the greatest battlefield, and the greatest victory is winning oneself"

ከሜሎሪና መጽሐፍ የተወሰዱ

_ሜሎሪና ገጽ 184 _

ታሪካዊ የሳይኮሎጂ ልብወለድ

...በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡ መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቊጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል፡፡ ሁሌም እንማር፣ ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንኹን፣ ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡

ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ዐዋቂ ነኝ፣ ትክክል ነኝ፣ እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይኾን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡

ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ሲኾን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይኾን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡

ታሪካዊ የሳይኮሎጂ ልብወለድ

ያነበቡት ኹሉ ወደውታል

የሜሎሪና መጽሐፍ ትረካ

Part1

Part2-3

Part 4-8

Part 9-15

Part 16-19