ናሁሰናይ ፀዳሉ
ሜሎሪና
ዐይን አላችሁ? ተመልከቱ! ጆሮ አላችሁ? እንግዲያውስ ስሙ! ልብ አላችሁ? አስተወሉ! ገንዘብ ምድራዊ ሕይወት እንጂ እውነተኛን ደስታን አይገዛላችሁም፡፡ ደስታን የሚገዛላችሁ እረፍት የሚሰጣችሁ ፈጣሪ ብቻ ነው፡፡ የሌለው ላይመጣ ያለው ላይሄድ ዕድሜያችሁን ሙሉ ከመባዘን ተጠበቁ!›› ይሉ ነበር አበምኔቱ፡፡
ናሁሰናይ ፀዳሉ
..በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡ መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቊጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል፡፡ ሁሌም እንማር፣ ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንኹን፣ ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡ ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ዐዋቂ ነኝ፣ ትክክል ነኝ፣ እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይኾን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡ ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ሲኾን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይኾን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡
በተለያዩ ሚዲያዎች የቀረቡ የመጽሐፉ ዳሰሳ
በEBS ቅዳሜን ከሰዓት፤በETV ፈታኝ ሳጥን በNahoo መዝናኛ፤ በአሐዱ ራዲዬ ፍኖተ ጥበብ ፕሮግራም፤ በFana ራዲዬ ጥበባት ፕሮግራም
በEBS ቅዳሜን ከሰዓት
Melorena Book Review on EBS kedame keseat ቅዳሜን ከሰዓት በኢቢኤስ | የሚሎሪና መጽሐፍ ዳሰሳ ከደራሲ ናሁሰናይ ፀዳሉ